Print Friendly, PDF & Email

የውስጥ ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ይገኛል

የመስፋፋት አዝማምያ እያሳየ ያለው የውስጥ ፖለቲካዊ ተዋናዮች የሆነ አላማ ላማሳካት አቅደው የሚያሰራጩት ሀሰተኛ መረጃ ለመታል አፍሪካ ውስጥ የመረጃ ማጣሪያን ማስፋፋት ከማህበራዊ ሚድያ ድርጅቶች በትብብር መስራት ያስፈልጋል።


English | Français | አማርኛ | العربية

ከአስመራ ወደ አቡጃ፣ ከሱዳን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ዲጂታል ሀሰተኛ መረጃ የተለመደ የአፍሪካ የውስጥ ፖለቲካ ምህዳር ባህሪይ የመሆኑ ጉዳይ እያደገ በመምጣት ላይ ነው ያለው።

እነዚህ ጥረቶች መጀመሪያ እንደ ሩስያ እና ሳውዲ አረብያ የመሳሰሉ የውጪ ተዋናዮች አፍሪካ ውስጥ ያስገቡዋቸው የተራቀቁ ዘዴዎችን ነው ሲጠቀሙ የነበሩት። ዲጂታል ሀሰተኛ መረጃ የሚያስከትለው የማዛባት እና የማምታታት ውጤት በመላ አህጉሪቱ የሚኖሩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ እና የደህንነት ክስተቶችን የሚከታተለውን የአፍሪካ ህዝብ እውነታዎች ከ “ሀሰተኛ ዜናዎች መለየት” አስቸጋሪ እንዲሆንበት የማድረግ ሁኔታው ከፍ እያለ ይገኛል።

የኦንላይን እምነት እና እውነት እየተበላሸ መምጣት ተጨማሪ የሴራ ትንታኔዎች ቦታ እያገኙ እንዲመጡ እና የተፈበረኩ ይዘቶች በዚህ በውዥምብር በተሞላ የመረጃ መድረክ ስር እንዲሰዱ አድርጓል። ሀሰተኛ መረጃ ክትባት መውሰድ ወይም የፖለቲካ ሂደት ውስጥ መሳተፍ በመሳሰሉ የአፍሪካውያን የእለት ተእለት ኑሮ የሚነኩ ጉዳዮች ላይ ሰዎች መረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎች እንዳይወስኑ እንቅፋት እየፈጠረባቸው ነው። የመጨረሻው የሀሰተኛ መረጃ አላማም ይህ ነው—በእነዚህ ሀሰቶች የሚጫወቱት አካላት ፖለቲካዊ አላማዎች ለማሳካት ሲባል ፍርሀትን እና ውዥንብርን መንዛት።

The Africa Center for Strategic Studies እነዚህን አዝማምያዎች እና የምያስከትሉዋቸው ጫናዎች ለመቀነስ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ደቡብ አፍሪካ መሰረት ያደረገው እና የ Atlantic Council’s Digital Forensic Research Lab (DFRLab) ተማራማሪ የሆነው Tessa Knight አናግሮ ነበር።

 *     *     *

እርስዎ ዩጋንዳ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ እና ሱዳን ስለ ሚከናወኑ ብዙ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎች ምርምር አድርገዋል ። ከእነዚህ ዘመቻዎች ጀርባ የነበረው አካል ማን ነው?

እኔ ጥናት ካካሄድኩባቸው የአፍሪክ ሀሰተኛ መረጃ አብነቶች ጀርባ ብዙ ተዋናዮች ናቸው የነበሩት። አንድ አይነት የሆኑ ኬዞች አላገኘሁም፣ ሆኖም ከእነዚህ አብነቶች አብዛኞቹ ሄደው ሄደው ከውስጥ መንግስታት ወይም ፖለቲካዊ ፓርቲዎች ጋር የተቆራኙ ሆነው ነው የተገኙት።

ኪንሻሳ ዩኒቨርሲቲ፣ DRC. (ምስል: Humprey J. L. Boyelo)

ከዩጋንዳው የጃንዋሪ 2021 ምርጫ በፊት፣ Facebook፣ Instagram፣ እና Twitter ላይ የተከፈቱ ማንነታቸው ያልተረጋገጡ የማህበራዊ ሚድያ መለያዎች በጥምረት በመሆን ገዢውን ፓርቲ በመደገፍ የተቀናጀ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ ነበር። ከእነዚህ መለያዎች ውስጥ የተወሰኑቱ {በመረጃ እና ተግባቦት ቴክኖሎጂ እና ብሄራዊ ምክር ሚኒስቴር ስር በሚገኘው የመንግስት ዜጋ መስተጋብር ማእከል (GCIC) አማካኝነት በቀጥታ የዩጋንዳ መንግስት ነበር የሚያንቀሳቅሳቸው። DFRLab ብያንስ አምስት ከ GCIC ጋር ቁርኝት ያላቸው የተጠቃሚ ግለ ማህደሮች ለይቶ ማወቅ የቻለ ሲሆን Facebook ጀንዋሪ 8, 2021 ኔትወርኩን በዘጋበት ጊዜ እንዲወገዱ ተደርገዋል።

ማንነታቸው አልተረጋገጡም ከተባሉት መለያዎች ብዙዎቹ የፕረዚደንት ሙሴቨኒ ወንድ ልጅ ቃለ አቀባይ እና የዩጋንዳ ጦር ሰራዊት ሌተናንት ጀነራል (እና የዩጋንዳ ህዝብ መከላከያ ኃይል የምድር ኃይሎች አዛዥ) ከሆነው Muhoozi Kainerugaba ጋር የተቆራኙ መሆናቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። ሌሎች በዩጋንዳ የሀሰተኛ መረጃ ኔትወርክ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መለያዎች ደግሞ የህዝብ ግንኙነት ተቋማት ወይም የዜና ድርጅቶች ናቸው ከተባሉ ቡድኖች ጋር የተቆራኙ ሆነው ነው የተገኙት።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ውስጥ ደግሞ፣ የኮቪድ ሀሰተኛ መረጃ በምናጣራበት ጊዜ ያገኘነው ማንነታቸው ያልተረጋገጡ መለያዎች ኔትወርክ በስተመጨረሻ ኪንሻሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሚገኝ የወጣቶች ቡድን ጋር የተቆራኘ ሆኖ ነው ያገኘነው። የዚህ ኔትወርክ ይዘት የኦንላይን ተከታዮች ማግኘቱን ተከትሎ—እና በማታለል—Honoré Mvula የሚባል ብሄራዊ ፖለቲከኛ ከማስተዋወቅ እና ከፍከፍ ለማድረግ እንዲሁም የእሱ Force des Patriotes የተባለው የእሱ የፖለቲካ ፓርቲ ለማስተዋወቅ እንዲችል ተደርጎ ሪብራንድ ተደርጎ ነበር። Honoré Mvula ከመለያዎች ጀርባ ካሉት ወጣቶች ጋር ቁርኝት እንደነበረው ኪንሻሳ ውስጥ በነበረ ፍጻሜ ላይ ከእነሱ ጋር አንድ ላይ ሆነው በተነሱዋቸው ፎቶግራፎች ለማረጋገጥ ችለናል።

“ብዙ ሰዎች ኣፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ያለው የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ደረጃ እና ምን ያህል የመረጃ ኔትወርኮችን እያዛባ እንደሆነ ግንዛቤው የላቸውም።”

ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የተቀናጀ የማህበራዊ ሚድያ ጫና በተመለከተ ያደረግነው የማጣራት ስራ እንደሚያሳው የአለማቀፍ ዳያስፖራ አባላት ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ በገለልተኛ አካል የተጣራ መረጃ በሌለበት ሁኔታ ተቃራኒ ትርክቶችን አንግበው ሰፋፊ የትዊተር ዘመቻዎችን ሲያካሂዱ ነበር። መንግስትን በመደገፍ ትዊት የሚያደርጉ መለያዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስ ደጋፊዎች እንዲጎሉ ሲደረግ ነበር።

በተዛማጅ፣ በትግራይ የኤርትራ ተሳትፎ የተመለከተ ፕሮፓጋንዳ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው በተባለ New Africa Institute (NAI) ተብሎ የሚጠራ ድርጅት የተፈጠረ ሲሆን፣ በኤርትራው የመረጃ ሚኒስቴር እና በብዙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ሲራገብ ነበር። NAI በስምኦን ተስፋማርያም ነው የሚመራው—እሱ አሜሪካ የሚኖር ሲሆን የታወቀ ወይም ግልጽ የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ማለትም የህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ደጋፊ ነው። እሱ ኮንፈረንስ ላይ የኤርትራ መንግስትን በመወከል ንግግር ሲያቀርብ የታየ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት የቅርብ ሰው ነው።

ሱዳን ውስጥ ማጣራት ያደረግንበት የሀሰተኛ መረጃ ኔትወርክ ከሩስያው ኦሊጋርክ  Yevgeny Prigozhin እና ከሩስያ የኢንተርኔት ምርምር ኤጀንሲ ጋር የተቆራኘ ሆኖ ነው የተገኘው። ይሁን እንጂ፣ Facebook ከኔትወርኩ ካስወገዳቸው 30 ገጾች ውስጥ 2 ብቻ ናቸው ከሩስያ ይመሩ የነበሩት። አብዛኞቹ ከሱዳን የሚመሩ ሆነው የተገኙ ሲሆን ምናልባት ሱዳን ውስጥ በሚገኙ በ Prigozhin የተቀጠሩ የሱዳን ዜጎች የሚመሩ ሊሆኑ ይችላሉ። Facebook ይህ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ከ Prigozhin-ጋር ግንኙነት ካላቸው ተቋማት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ አረጋግጧል፣ Facebook በ 2019 አስወግዶታል

እነዚህ ዘመቻዎች እንዴት ነው ሲመሩ የነበሩት?

ዩጋንዳ ውስጥ፣ ከተቀናጀው ሀሰተኛ ይዘት ጀርባ የነበረው ኔትወርክ በሶስት ክላስተሮች የሚከፈል ነው:

  1. ፕሬዚደንት ሙሴቬኒን እና ገዢው ብሄራዊ ተጋድሎ ንቅናቄ (NRM) ፓርቲን የሚደግፉ ልጥፎች
  2. ለፕረዚደንትነት ይወዳደሩ የነበሩት እጩ ተወዳዳሪ Robert Kyagulanyi (Bobi Wine) እና ደጋፊዎቻቸው የተመለከቱ ሀሰተኛ መረጃዎች ማሰራጨት
  3. የሙሴቬኒ ወንድ ልጅን የሆኑት

ሌተናንት ጀነራል Muhoozi Kainerugaba የመጪው ዘመን ፕሬዚደንታዊ እጩ እንደሚሆኑ ማራገብ። (ምስል: ትዊተር)

እያንዳንዱ ክላስተር ሀሰተኛ እና ተደራራቢ የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ እና ትዊተር መለያዎች የፈጠረ ሲሆን እነዚህ መለያዎች አሳሳች ምስሎች፣ ክሶች፣ እና ሃሽታጎች በመጠቀም ተቃዋሚዎችን የምያንኳስሱ መረጃዎች ለማሰራጨት ጥቅም ላይ ይውላሉ— ለምሳሌ ዩጋንዳ ውስጥ ያለውን የግብረሰዶማውያን ጥላቻ እንደ መልካም እድል በመጠቀም Bobi Wine ግብረሰዶማዊ ነው ብሎ ማስወራት። ክላስተሮቹ ልጥፎችን እና ሃሽታጎችን በመቅዳት በሀሰተኛ ተጠቃሚዎቹ ወደ ተፈጠሩ ብዙ ገጾች እና ቡድኖች ላይ በመለጠፍ አንዳቸው የአንዳቸው ሀሰተኛ ይዘቶችን ያራግባሉ። Facebook ገጾች ለሀሰተኛ ዜናዎች ሚድያ (“Kampala Times”) እና በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ግንኙነት ተቋም (“Robusto Communications”) ሀሰተኛ ይዘቱን የቅቡልነት ሽፋን በመስጠት ረገድ የእነዚህ ጥረቶች አካላት ሆነው ሰርተዋል። መጨረሻ ላይ፣ ጃንዋሪ 8, 2021፣ Facebook የመንግስት ጣልቃገብነትን የሚከለክለው ፖሊሲ ጥሰዋል በማለት 32 ገጾች፣ 230 የተጠቃሚ መለያዎች፣ 59 ቡድኖች፣ እና 159 የኢንስታግራም ግለ ማህደሮች አስወግደዋል። ትዊተር ከብዙ ቀናቶች በኋላ ከዚህ ኔትወርክ ጋር የተቆራኙ መለያዎችን አስወግዷል።

DRC ውስጥ ኪንሻሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት ተማሪዎች ብዙ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚድያ ግለ ማህደሮች ፈጥረዋል። Facebook መጨረሻ ላይ ከ Honoré Mvula እና የፖለቲካ ድርጅታቸው ጋር የተቆራኙ 66 የተጠቃሚ መለያዎች፣ 63 ገጾች፣ 5 ቡድኖች እና 25 የኢንስታግራም መለያዎች ያቀፈ ኔትወርክን አስወግዷል። ከእነዚህ ውስጥ 26 ገጾች እና 5 ቡድኖች በቀጥታ ከ 6 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን አረጋግጠናል። እነዚህን ገጾች pour le buzz,” እነሱ እንደፈጠሩዋቸው እና ስሜት ቀስቃሽ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን በመለጠፍ አንዳቸው ከአንዳቸው የበለጠ ተከታይ እና መውደዶች የማግኘት ፉክክር ውስጥ ገብተው እንደነበር ለአጣሪዎቹ ተናግረዋል።

በእነዚህ ገጾች ላይ የሚለጠፉ ልጥፎች ተመሳሳይ መንገድን ነው የሚከተሉት፤ አብዛኛው ጊዜ ልጥፉን “አስቸኳይ” ወይም “ሰበር ዜና!!” በማለት ይጀምሩታል። ልጥፎቹ DRC ውስጥ የሚገኙ ትምህርት-ቤቶች በሙሉ ያንን አመት ዝግ እንደሚሆኑ ከሚል የፈጠራ ወሬ እስከ ቢል ጌትን እና COVIDአፍሪካ ውስጥ የሚከናወኑ የኮቪድ-19 ክትባት ፕሮግራሞች የሚመለከቱ የሴራ ትንታኔዎች ያሰራጩ ነበር። ሀሰተኛ ይዘቶቻቸው በሂደት ብዙ ተከታዮች እያፈሩ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ፣ የገጾቻቸው ስሞችን ቀይረዋል—ካጠናናቸው 51 ገጾች ውስጥ አብዛኞቹ የዜና አውታሮች ወይም የፖለቲከኞች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፋዊ ገጾች አድርጎ ሪብራንድ ለማድረግ ከሚደረጉ ጥረቶች ጋር በተያያዘ ስሞቻቸው እንዲቀየር ተደርጓል። ሪብራንድ ከተደረጉ በኋላ፣ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ሀሰቶችን ማሰራጨት የቀጠሉ ሆነው የውስጥ የፖለቲካ ሀሰተኛ መረጃ ወደ ማሰራጨት ነው የዞሩት።

ከትግራይ ግጭት ጋር በተያያዘ የሚደረጉ የትዊተር ዘመቻዎች በአግረሲቭ የኦንላይን አክቲቪዝም እና በተቀናጀ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መካከል ያለውን ድንበር በማደብዘዝ ግልጽነት እንዳይኖር ያደረጉ ናቸው። የመንግስት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች ዳያስፖራዎች የትዊተር መለያ ለመፍጠር የሚያስችሉ ዝርዝር መመሪያዎች የሚሰጡ ድረገጾች ከፍተዋል ከዚያ በኋላ ደግሞ አስቀድመው የተዘጋጁ ጽሑፎች እና ሀሽታጎች ቀድተው ትዊት ለሚያደርጉ ተጠቃሚዎች ያቀርባሉ። ይህ “ጠቅ-አድርጎ-ትዊት ማድረግ” ዘመቻ ተብሎ ይጠራል። በተጨማሪ፣ የ NGOዎች፣ ጋዜጠኞች፣ እና አለማቀፍ ፖለቲከኞች የትዊተር መለያዎችም ተዘጋጅተው የቀረቡ ሲሆን፣ የዳያስፖራ አባላቱ እነሱን ታግ እንዲያደርጉ መመሪያ ተሰጥተዋቸው ነበር። አብዛኞቹ አስቀድመው- የተዘጋጁት መልእክቶች በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ ናቸው።

የሴራ ትንታኔን ከማምረት እና በኦንላይን ከማሰራጨት ጋር በተያያዘ፣ ማናቸውም ኤርትራ ትግራይ ውስጥ የፈጸመቻቸው ጥቃቶች የሚመለከቱ ማስረጃዎች የምእራባውያን ባለስልጣናት ኔትወርክ እና ከሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ቁርኝት ያላቸው ሪፖርተሮች ኤርትራን ለማጠልሸት የፈበረኩዋቸው ፈጠራዎች ናቸው ብሎ ለማሳመን የ NAI ሪፖርቶች የ “እውነታ-ማጣሪያ” የሚል ቋንቋ እና መግለጫ ሲጠቀሙ ነበር። ካጠናናቸው ሌሎች ዘመቻዎች በተለየ ሁኔታ፣ NAI “ሀሰተኛ መረጃ ትግራይ ውስጥ: ለተገንጣይነት ጦርነት ስምምነት መፈብረክ” በሚል አርእስት ስር በዝነኛው ራስ-አታሚ ድረገጽ አውታር ላይ 71-ገጽ ያለው ሪፖርት ለጥፏል። ይህ ሪፖርት ከትግራይ ጋር በተያያዘ ያለውን ሪከርድ እያረመ መሆኑ የሚገልጽ ቢሆንም፣ የኤርትራ ጦር ሰራዊት ትግራይ ላይ የፈጸማቸው በደሎችን ውድቅ ለማድረግ በማስረጃ ያልተደገፉ ክሶችን ሊረጋገጡ ከሚችሉ እውነታዎች ጋር ቀላቅሎ በአሳሳች መንገድ ሲያቀርብ ነበር። የኤርትራ ታሪክ እና ባህል የሚመለከቱ አጠቃላይ ሀሳቦችን የምያጣቅሱ የግርጌ ማስታወሻዎችን ተጠቅሟል—ለምሳሌ በደቦ ጾታዊ ጥቃት ማድረስ ኤርትራ ውስጥ አይታወቅም የሚል ድፍን መከራከርያ በማቅረብ—ለማሳመን ይሞክራል። ይህ ሪፖርት በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና በሌሎች የማህበራዊ ሚድያ መለያዎች ሲራገብ ነበር።

“ከ Prigozhin የተቆራኘው ኔትወርክ ከእነዚያ መለያዎች ውስጥ ብዙዎቹን የምያስኬዱ የሱዳን ነዋሪዎች በመቅጠር የመለያዎቹን ሀሰተኝነት የመታወቅ እድል ለመቀነስ እና መነሻቸው ከሩስያ እንደሆነ ለማወቅ ከባድ እንዲሆን ለማድረግ ሲሰራ ነበር።”

ሱዳን ውስጥ፣ ከ Prigozhin የተቆራኘው ኔትወርክ 83 ሀሰተኛ የ Facebook መለያዎች፣ 30 ገጾች፣ 6 ቡድኖች፣ እና 49 የኢንስታግራም ግለ ማህደሮች ፈጥረዋል። ለመለጠፍ፣ አስተያየት ለመስጠት፣ እና የራሳቸውን ይዘት ለ“መውደድ” እንዲሁም በብዛት የሱዳን ፖለቲከኞች እና የሚድያ ድርጅቶች መሆናቸው የሚገልጹ ሀሰተኛ ገጾችን—ለማስተዳደር ይጠቀሙባቸዋል። መለያዎቹ አብዛኛው ጊዜ ሀሰተኛ የግለ ማህደር ምስሎችን ለመፍጠር የተራቀቁ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ከእነዚያ መለያዎች ውስጥ ብዙዎቹን የምያስኬዱ የሱዳን ነዋሪዎች በመቅጠር የመለያዎቹን ሀሰተኝነት የመታወቅ እድል ለመቀነስ እና መነሻቸው ከሩስያ እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ እንዲሆን ለማድረግ ሲሰሩ ነበር። ይህ የስታንፎርድ ተመራማሪዎች በ 2019 ሱዳን ውስጥ ካገኙት የ “ፍራንቻይዚንግ” ዘዴ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ነው የተገኘው። በአረብኛ (አንዳንድ ጊዜ በትክክል ያልተተረጎመ ይዘት በዘፈቀደ መቅዳት እና መለጠፍ) ነው ሲለጥፉ የነበረው። አብዛኞቹ ልጥፎቻቸው ስለ ሩስያ እና Prigozhin በሱዳን ውስጥ መኖር አወንታዊ ወሬዎች የምያወሩ ሲሆን፤ ይህ ሱዳን ውስጥ በ Prigozhin ለሚሰራጩ “ከሩስያ ከፍቅር ጋር” የሚል መገለጫ ለተለጠፈባቸው የእርዳታ ጥቅሎች ብዙ ትኩረት እንዲሰጣቸው ማድረግን የምያካትት ነበር። ሌሎች ወሬዎች ደግሞ ሱዳን የሩስያ ወታደራዊ ቤዝ ፖርት ሱዳን ላይ ማስተናገድዋ የምያስገኝላት ጥቅሞች ላይ ያተኮሩ ነበሩ።

የእነዚህ ዘመቻዎች አላማዎን ምንድን ነበሩ?

ዩጋንዳ ውስጥ ጃንዋሪ 2021 እስከ ተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ፣ የፕረስ ነጻነት በጣም ታፍኖ ነበር። ስለዚህ፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ በተለይም በ Bobi Wine የብሄራዊ ሕብረት መድረክ (NUP) የሚመራው የወጣቶች ንቅናቄ፣ መረጃን ለማጋራት እና ምርጫዎቹ በተመለከተ የማደራጃ ዝማኔዎችን ለማቅረብ ወደ ማህበራዊ ሚድያ ነበር የተመለሱት። አነፍንፈን ያገኘናቸው የገዢው ፓርቲ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጫ ኔትወርኮች ቦብ ዋይንን በማንኳሰስ እና ለሙሴቬኒ የሚደግፉ ልጥፎች በመለጠፍ የተቃዋሚው የማህበራዊ ሚድያ ጥረቶች እና እያደገ የመጣው የ NUP ዝና ዝቅ ለማድረግ ወይም ለማሳነስ ሲሞክሩ ነበር።

የሞባይል ስልክ ባትሪ መሙያ ጣብያ ዩጋንዳ ውስጥ። (ምስል: AdamCohn)

DRC ላይ፣ ሀሰተኛ መለያዎቹ ከ “clickbait” ቅቡል ወደ ሚመስሉ የዜና ድርጅቶች እና የፖለቲካ ገጾች ከተቀየሩ በኋላ፣ Honoré Mvula ን በመደገፍ አወዳሽ ወሬዎችን ስያሰራጩ ነበር። ይህ ዋንኛው የ 2018 ፕሮዚደንታዊ ምርጫ የተቃውሞው ጎራ ተወዳዳሪ የሆነው Martin Fayulu፣ በአንድ-ጊዜ ተፎካካሪው የነበሩት ፕሬዚደንት Félix Tshisekedi ስልጣናቸው ከተረከቡ በኋላ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በማለት ሲከሳቸው ነበር የሚሉ ሀሰተኛ ወሬዎችን የምያካትት ነበር።

የኢትዮጵያዎቹ “ጠቅ-አድርጎ-ትዊት ማድረግ” ዘመቻዎች አውድ መንግስት ኢንተርኔትን ከቆረጠ እና የሚድያ ተደራሽነትን ከከለከለ በኋላ ትግራይ ውስጥ ስለሚከናወኑ ነገሮች የመረጃ እጦት ተከስቷል የሚል እውነታ መነሻ ያደረጉ ናቸው። ይህ ለሀሰተኛ መረኛ የሚመች ሁኔታን ፈጥሯል። በሁለቱም ወገን ያሉ የዳያስፖራ ቡድኖች ትግራይ ውስጥ በተጨባጭ መሬት ላይ ስለ ነበረው ጉዳይ የትርክቶች የበላይነት ለመያዝ ይሞክሩ ነበር። ትዊተርን በመጠቀም እና ተጽእኖ ፈጣሪ ተጠቃሚዎችን ታግ በማድረግ፣ ምንም እንኳ ሁለቱም አካላት ትግራይ ውስጥ በተጨባጭ መሬት ላእ ስለ ነበረው እውነታ ትክክለኛ ወይም እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የሌላቸው ቢሆንም፣ የአለማቀፍ ተዋናዮች አመለካከት ለመቅርጽ ይፈልጉ ነበር።

ኤርትራ እና ኢትዮጵያ የ NAI ሪፖርትን ከመንግስት-ግር ቁርኝት ባላቸው የማህበራዊ ሚድያ መለያዎች አማካኝነት ለምያሰራጩት የተለመደ ወይም ባህላዊ ፕሮፓጋንዳ ተጠቅመውበታል። የእነዚህ ባለስልጣናት ፍላጎት ሪፖርቱን እንደ “ገለልተኛ” አድርገው ለመጠቀም እንዲሁም “በእውነታ-ማጣሪያ” ያለፈ ሰነድ በማስመሰል የንግግር መነሻ ሀሳቦችን እሱ ላይ ተመስርተው ለመፍጠር የኤርትራ ተሳትፎ በትግራይ በተመለከተ ለምያቀርቡዋቸው መከራከሪያ ነጥቦች ሰነዱን እንደ ማጣቀሻ የመጠቀም ፍላጎት የነበረ ይመስላል። የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ እየተዋጉ እንደሆነ እና ግፎችን እና ወሲባዊ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ መሆናቸውን በተመለከተ የሚመጣው አለማቀፍ ውግዘት ውድቅ ለማድረግ ወይም ለማጣጣል ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ያሉት ምእራባውያን ባለስልጣናት ናቸው የሚል መከራከርያ ለማቅረብ ባለስልጣናቱ ተጠቅመውበታል።

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ የሚሰሩ ባለስልጣናት የስምኦን ተስፋማርያምን ስራ እና የ NAI ትግራይ ሪፖርት ጠቅሰው እንዲከራከሩ የምያበረታታ የተባለ የድምጽ ቅጂም አግኝተናል:

“ጓድ ስምኦት ተስፋማርያም፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች እኛን በመከላከል ማብራሪያ ሲሰጥ አይተሀዋል። ይህንን የተነሱት ጉዳዮችን በሙሉ ውድቅ የምያደርግ፣ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገቡ የምያደርግ፣ እና እነሱን የሚሞግት ጠንካራ ጥናታዊ ጽሑፍ አዘጋጅቷል። እንደገና፣ ስሙን የጠራሁት ለማበረታታት ብቻ ነው። ጽሑፉ ወይም መጣጥፉ በ New Africa Institute ነበር የተለቀቀው። በ New Africa Institute እንዲለቀቅ የተደረገበት ምክንያት ስልታችን አላማውን ሙሉበሙሉ እንዲመታ ለማድረግ ነው፣ አንዱ የመግቢያ መንገዳችን ይህንን ነው መምሰል ያለበት። በተቋም እና በግል ደረጃ የምሰራቸው ስራዎች ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ፣ የራሳችን የሆኑ የምርምር ማእከላትን መመስረት አለብን፣ ወይም ዜጎቻችን የግድ ይዘቱን መፍጠር አለባቸው።” [ከትግርኛ የተተረጎመ]

የሱዳኑ Prigozhin የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጫ ኔትወርክ አላማ ሩስያን እና Prigozhin ን የሱዳን ወዳጆች እንደሆኑ ማራገብ ነው የነበረው። በተጨማሪም የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎችን (የሉአላዊነት ምክር-ቤት ምክትል ሊቀመንበር በሆኑት በጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራ) ለመደገፍ እና ሌሎቹን የሱዳን ሽግግር መሪዎች እንደ የአሜሪካ ተላላኪዎች አድርጎ የመሳል ፍላጎት ያለው ሆኖ ሱዳናውያን በአምባገነኑ ኦማር አል-በሽር የአገዛዝ ዘመን የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደነበሩ እስከ ማሳሰብ የደረሱ ሀሳቦችን ይሰነዝር ነበር። ሩስያ በፖርት ሱዳን የባህር ኃይል ቤዝ እንድትገነባ የመፍቀድ እቅዱ ተግባራዊ ሳይደረግ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ፣ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቱ መልእክቶች ሁልጊዜ የሱዳኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚተቹ የኋላኋም የላአላዊ ምክር-ቤት ሊቀ-መንበር የሆኑት ሌተናንት ጀነራል አብደል ፋታህ አብደልራህማን አል-ቡርሃንን የሚተቹ ሆነው ነበር።

የእነዚህ ዘመቻዎች ውጤቶችን እና ያስከተሉዋቸው ጫናዎችን በተመለከተ ያሎት ግምገማ ምን ይመስላል?

ዩጋንዳ ውስጥ፣ ከመንግስት-ጋር የተገናኘው የሀሰተኛ መረጃ ዘመጃ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ውጤት አስከትሏል። ይህ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ አጨቃጫቂው ምርጫ ላይ በምን መንገድ ጫና አሳድሮ ሊሆን እንደሚችል ለመናገር አስቸጋሪ ቢሆንም፣ የሀሰተኛው ይዘት ተደራሽነት ማህበራዊ ሚድያ ላይ እስከ ድምጽ መስጫ ቀኑ ድረስ በነበሩ ጊዜያት ሰፊ ነው የነበረው። የኔትወርኩ አካል የነበሩት የህዝብ ግንኙነት ተቋማት በድምር ከ 10,000 በላይ መለያዎች ይከተሉዋቸው ነበር። Facebook የኔትወርኩን የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ማስወገዱ፣ በበኩሉ፣ የሙሴቬኒ አገዛዝን ኢንተርኔትን እንዲዘጋ እና ሴስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም፣ እና ትዊተርን ምርጫው ቀናቶችን ሲቀሩት እንዲዘጋ አነሳስቶታል። ብዙ ዩጋንዳውያን ዜናዎችን የምያገኙ ከማህበራዊ ሚድያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ይህ በወሳኝ ጊዜ መረጃ የማግኘት እድላቸው ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል። ይህንን ተከትሎ የፕሬዚደንት ሙሴቬኒ ከፍተኛ የፕረስ ሴክሪተሪ የሆኑት ዶን ዋንያማ የዩጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚሽን ከምርጫው በ ኋላ ለ 6 ወራት ተዘግቶ የቆየው ፌስቡክን እንዲመረምር ጠይቋል። መንግስቱ እገዳውን ጥሰው ሊያልፉ የሚችሉ ቨርችዋል ፕራይቬት ኔትወርኮችን (VPNs) ጭምር ዘግቷል።

“ዩጋንዳ ውስጥ፣ ከመንግስት-ጋር የተገናኘው የሀሰተኛ መረጃ ዘመጃ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ውጤት አስከትሏል. … የሀሰተኛው ይዘት ተደራሽነት ማህበራዊ ሚድያ ላይ እስከ ድምጽ መስጫ ቀኑ ድረስ በነበሩ ጊዜያት ሰፊ ነው የነበረው።”

DRC ላይ Facebook የዘጋቸው ሀሰተኛ ገጾች 1.5 ሚልዮን “መውደዶች” መሰብሰብ ችለው ነበር፣ ስለዚህ በጣም ብዙ ህዝብ ጋር ይደርሱ እንደነበር ግልጽ ነው። እነዚህ የሚያሳዩት የውስጥ ፖለቲከኞች ሰፊ ተከታይ ያገኙ ገጾችን አጭበርብረው ከቁጥጥር ስራቸው በማስገባት እና ለፖለቲካ አላማ ማስፈጸሚያ በማዋል ምን ያህል የሀሰተኛ መረጃ ተደራሽነት ላይ ሰፊ ስራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ነው።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ያሰናዱዋቸው “ጠቅ-በማድረግ-ትዊት ያድርጉ” ዘመቻዎች ኬዝ ያየን እንደሆነ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እና ፖሊሲ አውጪዎችን ተጋላጭ ያደረጉ በጣም ብዙ የተሳሳቱ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎች መኖራቸውን እንረዳለን። ሌላው ውጤት ከትግራይ (ኢንተርኔት የተዘጋበት ቦታ) ውጪ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ምንጫቸው ከዳያስፖራው የሆኑ መንግስትን የሚደግፉ ትርክቶችን ለመጠቀም እና ለማሰራጨት ትዊተርን መጠቀም በመጀመራቸው ተከትሎ ኢትዮጵያ ውስጥ በእነዚህ ዘመቻዎች ጊዜ ትዊተር መጠቀምን ከፌስቡክ መጠቀም በላይ ማደጉ ነው። ይህ ምሳሌ በተቀናጀ አክቲቪዝም (ይህ ባለፈው አመት በነበሩት የናይጄርያ #EndSARS ተቃውሞዎች ላይም ታይቷል) እና በተቀናጀ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ መካከል ያለውን መስመር በጣም ቀጭን መሆኑን የሚያሳይ ነው። የተጋነኑ እና ያልተረጋገጡ ወይም ያልተጣሩ መከራከርያዎች ወይም ክሶች ሆን ተብሎ ወደ ሚሰራጩ ሀሰቶች የመሸጋገራቸው ነገር አይቀሬ ይሆናል፣ መቼ ይሸጋገራሉ ብቻ ነው ጥያቄው።

በስምኦን ተስፋማርያም የቀረበው የ NAI ሪፖርት የፈጠረው ተጽእኖ በቁጥር ማስቀመጥ ከባድ ቢሆንም፣ ሪፖርቱ በኮሜድያን እና ተዋናይት ቲፋኒ ሐድሽ (በ 2019 የኤርትራ ዜግነት የተሰጣት) አማካኝነት ወደ ብዙ ታዳሚዎች እንዲደርስ ተደርጓል። የእሷ አራጋቢነት NAI የንግግር መድረኮች እና ሚድያ ላይ እንዲታደም አስችሏል። የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ባለስልጣናት የ NAI ጥረቶችን የመጠቀማቸው እና ሌሎች እነዚህን የሚመስሉ ጥረቶች ማበረታታቸው የሚያሳየው እንዴት የመረጃ-ማጣሪያ መገለጫዎች በተሳሳተ መንገድ “የመረጃ-አጣሪዎችን መረጃ-በማጣራት” በተሳሳተ መንገድ ለማከናወን እንደ ማጠናከሪያ በመጠቀም እውነታ ደባቂ መንግስታት በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፉ ክሶችን ለመሞገት ምቹ ሁኔታ ሊፈጥሩላቸው እንደሚችሉ ነው።

ሱዳን ውስጥ የታዘብነው የሀሰተኛ መረጃ ኔትወርክ ከ 440,000 መለያዎች በላይ ይከተሉት ነበር። ስለዚህ፣ ልጥፎቹ ብዙ ጊዜ በዘፈቀደ የተተረጎሙ ቢሆኑም እንኳ ሰፊ ታዳሚዎችን መድረስ ችሏል። ሆኖም፣ የዚህ ዘመቻ ተጽእኖ ለመገምገም አስቸጋሪ ነው።

ምናልባት ግንኙነት ከነበረ፣ በእነዚህ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እና አፍሪካ ውስጥ በአለማቀፍ የገንዘብ ድጋፍ በሚደረገው የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ መካከል የነበረው ግንኙነት ምን ይመስላል?

ሱዳንን በተመለከተ አለማቀፋዊ (ማለትም፣ ሩስያ) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ከሃገር ውስጥ በተቀጠሩ ስራ አስኪያጆች አማካኝነት እንዲደበቅ የማድረግ ሙከራ እንደበር በግልጽ ታይቷል። በጥናታችን ውስጥ ከተካተቱት ኬዞች ውስጥ ይህንን ምሳሌ እና የትግራይ ግጭት በተመለከተ ትርክቱን ወደ ሚፈልጉት አቅጣጫ ለመግራት በሚደረግ ሙከራ የነበረው የዳያስፖራው ተሳትፎ ብቻ ናቸው አለማቀፍ ትስስር ያገኘንባቸው።

ከስፋት፣ ዘዴዎች፣ እና ተጽእኖ አንጻር በእነዚህ ዘመቻዎች እና አፍሪካ ውስጥ በአለማቀፍ ተዋናዮች በሚደረጉት ዘመቻዎች መካከል ምን መመሳሰሎች እና ልዩነቶችን ነው ያገኙት?

ቻይና እና ሩስያ አፍሪካ ውስጥ ምን እያደረጉ እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች መልእክቶችን ይልኩልኛል። መልካም፣ የአፍሪካ ሀጋራትስ አፍሪካ ውስጥ ምንድነው እያደረጉ ያሉት? ብዙ ጊዜ የአፍሪካ ሀገራት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተራቀቀ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ማድረግ የማይችሉ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች ያሉ ይመስለኛል። ይህ አስተሳሰብ በአህጉሪቱ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የኦንላይን ተዋናዮች ችሎታን እንዲሁም ሰዎች አጀንዳዎቻቸውን ከግብ ለማድረስ የሚጓዙት ርቀት በሰፊው አሳንሶ የሚያይ ነው። አፍሪካ ውስጥ በመቶ ሚልዮኖች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እና የትዊተር ተጠቃሚዎች አሉ። የተቀናጀ የሀሰት መረጃ ስርጭት በምርቡ አለም ወይም በእስያ ሀገራት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም።

እኔ ማጣራት ያደረግንባቸው ኬዞች ከዚህ ቀደም አፍሪካ ውስጥ ካገኘናቸው አለማቀፋዊ ዘመቻዎች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ነው የምለው። ዋነኛው ልዩነት ከሀገር ውስጥ ወይም ከዳያስፖራው አባላት የተነሱት ዘመቻዎች ኢላማ የምያደርጉዋቸው ሃገራት ቋንቋ እና ባህል የማወቅ ዕድል ያላቸው መሆኑ ነው። DFRLab በጥናቱ ባገኛቸው ኬዞች፣ ሩስያ እንደ ሱዳን በመሳሰሉ ሃገራት ይዘቶችን የሚተረጉሙ እና የሚለጥፉ የሃገር ውስጥ ተዋናዮችን የምትቀጥር ቢሆንም፣ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የምታደርገው የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት እውነተኛ ለማስመሰል ከፍተኛ ጥረት እንደምታደርግ ታይቷል። በ DRC እና Uganda ኬዞች፣ የሃገር ውስጥ ተዋናዮች የበለጠ እድል ነበራቸው፣ ምክንያቱም አውዱን ያውቃሉ፣ ቋንቋውን ያውቃል፣ እንዲሁም ብዙ በቀላሉ የማይታዩ የፖለቲካ ልዩነቶችን ጭምር ያውቃሉ። የበለጠ አሳማኝ ይዘትን ወጥ በሆነ መንገድ መፍጠር ይችላሉ።

ያጠኑዋቸው ዘመቻዎች አፍሪካ ውስጥ የሚካሄደው የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ ዋነኛ ተዋናዮችን ያንጸባርቃሉ?

ሁሉም ያጠናሁዋቸው ኬዞች ዲጂታል ሀሰተኛን የምያመርቱ ወይም ከዚሁ የሚጠቀሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወይም አገዛዞችን ያሳተፉ ናቸው። ሆኖም ይህ እኔ ያጠናሁዋቸው ጉዳዮች የአፍሪካ ምርጫዎች እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ አለመረጋጋቶችን የሚመለከቱ የመሆናቸው እውነታ ተጽእኖ አድርጎበት ሊሆንም የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው። አብዛኞቹ እና በጥልቀት የመረመርኳቸው የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎች ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ያነገቡ ናቸው።

ጥናት ያካሄዱባቸው ዘመቻዎች በአፍሪካ ዲጂታል ምህዳር ውስጥ በአንጻራዊነት ለየት ያሉ ናቸው ወይስ አህጉሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣው ሀሰተኛ ይዘትን በተቀናጀ መንገድ የማስፋፋት አካሄድ ማሳያ መገለጫዎች ናቸው? በአንጻራዊነት የበለጠ በዚህ ተጽእኖ ስር የገቡ አካባቢዎች ወይም ሃገራት አሉ?

እኛ በጥናታችን ያገኘነው የተቀናጀ ሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ መጠን ከባህር በጭልፋ ነው እንዲሁም መንግስታት እና ፖለቲከኞች ማህበራዊ ሚድያን በሀሰተኛ፣ ተደራራቢ፣ የተቀናጀ ይዘት ምርት አማካኝነት ለአላማቸው የማዋል ስልትን እያወቁ በመጡ ቁጥር የበለጠ እየሰፋ የምሄድ ነው ብየ ነው የምጠረጥረው።

“ከምርጫ ወይም ከግጭቶች ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የተደረገ የተቀናጀ የሀሰት መረጃ መኖሩን ለማግኘት ሞክሬ፣ ሳላገኝ ቀረሁበት ጊዜ የለም።”

ከምርጫ ወይም ከግጭቶች ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የተደረገ የተቀናጀ የሀሰት መረጃ መኖሩን ለማግኘት ሞክሬ፣ ሳላገኝ ቀረሁበት ጊዜ የለም። ሰለ አፍሪካ የኦንላይን ምህዳር ያደረግኩት ጥናትም ያገኘሁት ሀሰተኛ መረጃ ዘመቻም የለም።

ብዙ ሰዎች ኣፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ያለው የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ደረጃ እና ምን ያህል የመረጃ ኔትወርኮችን እያዛባ እንደሆነ ግንዛቤው ያላቸው አይመስለኝም። የስራ ባልደረቦቹ ሌሎች ከ ቱኒዝያ (የቱኒዝያ፣ ቶጎ፣ እና ኮትዲቫር ምርጫዎችን ኢላማ ያደረጉ)፣ ጊኒ፣ ኬንያ፣ እና ደቡብ አፍሪካ የሚሰራጩ ዘመቻዎችን አጥንተዋል።

የበለጠ በአጠቃላይ ሲታይ እነዚህን አፍሪካ ውስጥ የሚካሄዱ ዘመቻዎች እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶች ምን ጥያቄ ያጭሩቦታል?

እንደ ዩጋንዳ የመሳሰሉ ሃገራት ውስጥ ከሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎች ጋር ቁርኝት ያላቸው የምንግስታት ባለስልጣናት ከማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ማወቅ መቻል አፍሪካ ውስጥ ስላለው የውስጥ ሀሰተኛ መረጃ ዘመቻ፣ እንዴት እየተመረተ እንደሆነ፣ እና ማን እንደሚመራው የመሳሰሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ለመመለስ የሚረዳ ይመስለኛል።

በአፍሪካ ዲጂታል ምህዳሮች ውስጥ ሀሰተኛ ወይም እውነተኛ ያልሆነ ይዘት ለመቆጣጠር፣ ለመከላከል እና ለማስወገድ ምንምን ስኬታማ ጥረቶች ሲደረጉ አዩ?

በአሁኑ ጊዜ በጋራ በመሆን እና ከ Facebook ጋር በመስራት ኦንላይን ላይ ካሉት አስቀያሚ እና ሰፊ ስርጭት ያላቸው የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶች የተወሰኑትን ለመከታል እና ለማጋለጥ የሚሰሩ እንደ Africa CheckPesa CheckMedia Monitoring Africa, እና iLab የመሳሰሉ የመረጃ-አጣሪ ድርጅቶች አሉ። በተመሳሳይ፣ Facebook አሁን አንዳንድ ተመሳሳይ ቅጂዎች እና በግልጽ የሚታወቁ ሀሰተኛ መለያዎች እና ገጾች በራስ-ሰርነት ወይም በአውቶማቲክ መንገድ መዝጋት ጀምሯል። ሆኖም፣ እኔ እንዳልኩት፣ ይህ ከባህር በጭልፋ ነው።

“አስደናቂ ጋዜጠኝነት እና የሀሰተኛ መረጃ ሪፖርቶች ከአህጉሪቱ መውጣት በጀመሩበት በዚህ ጊዜ እንደነዚህ አይነት ጥናቶች የምያካሂዱ የሃገር ውስጥ ድርጅቶች እየበዙ ናቸው።”

ጥቂት ሰዎች ነን የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎችን በጥልቀት በመመርመር እና ምንጫቸውን፣ ማስፈንጠሪያዎቻቸውን፣ እና ተደራሽነታቸውን ለማወቅ በንቃት እያነፈነፍን ያለነው። እነደዚህ አይነት የኦንላይን ምርመራ እና የመረጃ ማቀበል ስራ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጣም ሰንሲቲቭ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ ሁሉም ቦታዎች ላይ አይደለም እየሆነ ያለው። በተጨማሪም የእነዚህን ዘመቻዎች ሽፋን በመግለጥ በጥልቀት ገብቶ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ስልጠና እንዲሁም ከፌስቡክ እና ትዊተር ጋር ዝምድና መፍጠር እና እነሱ ብቻ የምያገኙዋቸው መረጃዎች እንድያጋሩን የእነሱ ፈቃደኝነት መሻት ያስፈልጋል።

እኔ እና ጥቂት ሌሎች እያደረጉት ያለው የኦንላይን ምርመራ ሥራ ሊባዛ እና ሊስፋፋ የሚችል ይመስለኛል። ዲጂታል የፎረንሲክ ምርምር ላብራቶሪው በአህጉሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማህበራት አባላቶች፣ እና ተመራማሪዎች የዲጂታል ሀሰተኛ መረጃ ኔትወርኮችን ማጋለጥ እና ማጥናት የሚችሉባቸው ክህሎቶች እንዲጨብጡ ለማገዝ፣ በ 360/Digital Sherlocks ፕሮግራማችን አማካኝነት ብዙ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን ይሰጣል።

እንዳለመታደል ሆኖ፣ በአፍሪካ ሃገራት ውስጥ የሀሰተኛ መረጃ ሁኔታን ለማጣራት ወይም ለማጥናት ብዙ ፍላጎትም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ የለም። ሆኖም አስደናቂ ጋዜጠኝነት እና የሀሰተኛ መረጃ ሪፖርቶች ከአህጉሪቱ መውጣት በጀመሩበት በዚህ ጊዜ እንደነዚህ አይነት ጥናቶች የምያካሂዱ የሃገር ውስጥ ድርጅቶች እየበዙ ናቸው። እኔ ሁሉም ለማመን በሚከብድ ደረጃ አደገኛ ሊሆን በሚችል ሁኔታ ውስጥ በጨቋኝ መንግስታት ስር ሆነው ይህንን ስራ ለሚሰሩ ተመራማሪዎች እና ጋዜጠኞች አክብሮት አለኝ።

እርስዎ እነዚህ ተነሳሽነቶች እንዴት ሊታገዙ፣ ሊስፋፉ፣ ወይም ሊባዙ እንደሚችሉ በማስመልከት የምያቀርቡዋቸው የፖሊሲ ምክረ-ሃሳቦች አሉ?

የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች አፍሪካ ውስጥ የበለጠ ኢንቨስት ማድረግ አለባቸው። እየሰሩባቸው የሚገኙባቸው የአፍሪካ ሃገራት እና የተለየ ባህሪይ ያለው የመረጃ እና ፖለቲካ ምህዳራቸው በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ወይም አረዳድ የላቸውም። ይህ ሀሰተኛ መረጃን በተመለከተ መጥፎ ውሳኔ እንዲወስኑ እና አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች ከመስራት ይልቅ ከሆነ በኋላ ምላሽ የሚሰጡ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በተመሳሳይ፣ ተመራማሪዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ እና ሪፖርቶሮች እነዚህን የሀሰተኛ መረጃ ኔትወርኮች እና ከጀርባቸው ያሉ አካላትን መረዳት እንዲችሉ ከ Facebook የበለጠ መረጃ ያስፈልጋቸዋል።

በተጨማሪም ለማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች የሚሰሩ የአፍሪካ ውስጥ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር መብዛት አለበት። ጥቂት ቋንቋዎች ብቻ በመጠቀም ውጤታማ የማህበራዊ ሚድያ ሚዛን ሊኖርህ አይችልም። ይህ ትንሽ አስቸጋሪ እንደሆነ ይገባኛል፣ ምክንያቱም ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ 11 የስራ ቋንቋዎች አሉን። ሆኖም በሚልዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ኦንላይን ከመሆናቸው እና የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች የእነዚህን ገበያዎች ዋጋ በግልጽ እያዩ ከመሆናቸው አንጻር ተጨማሪ ሃብት አፍሪካ ውስጥ ማፍሰስ ያስፈልጋል ብየ አስባለሁ።

ከአፍሪካ ትልልቅ ዲሞክራሲዎች አንዳንዶቹ የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ሀሰተኛ መረጃን በመቆጣጠር ረገድ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እና ግኝቶቻቸውን በግልጽነት በማጋራት ገበያዎቻቸው ላይ እንዲንቀሳቀሱ እነደ አንድ ፈቃድ ማግኛ መንገድ እንዲጠቀሙባቸው ጥሪ ቢያቀርቡ ጠቃሚ ይሆን ነበር።

የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎቹ ጥረቶቻቸውን ከፍ እንዲያደርጉ እንፈልጋለን ምክንያቱም አፍሪካ ውስጥ ሀላፊነቱን ለመንግስት መተው ጉዳቱ ለራሳቸውም ሊተርፍ ይችላል። እንደ ናይጄርያ፣ ዩጋንዳ፣ ወይም ደቡብ አፊሪካ የመሳሰሉ ሃገራት ሀሰተኛ መረጃን ወንጀል ለማድረግ ሲሞክሩ አይተናል፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ለማፈን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። እነዚህ ሕጎች ሌሎች ለፕረስ፣ መሰብሰብ፣ እና ንግግር ነጻነት መድረኮች እየተዳከሙ ባሁሉበት በአሁኑ ጊዜ ኦንላይን ላይ የመደራጀት እና መረጃ የማጋራት እድላቸውን እያሰፉ ባሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ማፈኛ ዘዴ ተደርገው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።


ተጨማሪ ማጣቀሻዎች