በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ውጥረቶች አና የቀጠናዊ ግጭት ስጋቶች

በትግራይ የፖለቲካ መሪዎች መካከል ያሉ ክፍፍሎች ትግራይን ወደ ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መዋቅር የመቀላቀል ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሲሆን ኤርትራን እና ለሎች ክልሎችን ወደሚያሳትፍ ሰፊ ግጭት በፍጥነት ሊያመራ ይችላል።


English | Français | አማርኛ

የድንበር ውስጥ ተፈናቃዮች በጸሀዬ ተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የትግራይን ባንዲራ አልፈው ሲራመዱ። (ፎቶ፦ ኤኤፍፒ/Michele Spatari)

የትግራይ የሽግግር ባለስልጣን አመራርን በተመለከተ ውጥረቶቹ በፍጥነት እየተባባሱ በመምጣቱ ውዝግቡ በፍጥነት ወደ ክልላዊ ግጭት ሊሸጋገር ይችላል የሚሉ ጭንቀቶች ክልሉን በጭንቀት ወጥረዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል wede 600,000 የሚገመቱ ሰዎች የሞቱበት ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም ከተደረገ ከ2 ዓመታት በላይ ሲሆን ትግራይ በከፍተኛ ደረጃ ተበታትና በክልሉ እንዳሉ ከሚገመተው 7 ሚሊዮን ነዋሪዎች መካከል 15 በመቶው አሁንም ተፈናቅሏል።

አሁን ያለው ቀውስ ካለፈው አመት ጀምሮ በህወሓት ውስጥ በተፈጠሩ የሰልጣን ፉከከር የተነሳ ጫና ነው። እነዚህ ውጥረቶች የህወሓት መሪ በሆነው  (ዶ/ር) ደብረፂዮን ገብረሚካኤል  እና የቀድሞ ምክትላቸው በነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር (TIA) ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትችቶች ዙሪያ ያተኮረ ነው። እኤአ በኖቬምበር 2022 ተፈርሞ በፌዴራል መንግስት እና በህወሀት መካከል ለ2 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት ያስቆመውን የጦርነት ማቆም ስምምነት (COHA) ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያሳዩትን መጏተት በተመለከተ ደብረጽዮን ጌታቸውን እና ጊዝያዊ TIA ኣስተዳደርን ተጠያቂ አድርጓል። ደብረጽዮን TIA እንዲፈርስ ጠይቀውሥልጣኑን ለማናናቅ ሞክረዋል። TIA የተቋቋመው በCOHA ስር የትግራይን መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አወቃቀር መመለስ የሚመራ ጊዜያዊ ባለስልጣን ሆኖ እንዲያገለግል ነው። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በትግራይ ተወላጆች ዘንድ ተአማኝነት ያለው በመሆን የህወሃት ከፍተኛ አመራር ሆኖ ጊዜያዊ አካሉን እንዲመራ አቶ ጌታቸውን ሹመው ነበር።

በፍጥነት እየጨመሩ ያሉትን ውጥረቶች ለማርገብ /ሚ አብይ እኤአ ማርች 26 ላይ አቶ ጌታቸው የ(TIA) ፕሬዝዳንትነት እንደሚለቁ አስታውቋል። የእርሳቸው ምትክ ገና አልተሰየመም። ይህ እርምጃ የትግራይን ሽግግር ለማደናቀፍ የሚያሰጋውን ውጥረት የሚያረግብ ከሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

የሰሞኑ መባባስ መንስኤው የትግራይ መከላከያ ሃየልን (TDF) ለመቆጣጠር በተፈጠረ አለመግባባት ላይ ነው። የህወሓት የረዥም ጊዜ አመራር የነበረው ደብረፂዮን ስልጣን በTIA ስር አይወድቅም ሲሉ ተናግረዋል። ወጣት የህወሓት አመራር አባላትን በመወከል አቶ ጌታቸው፣ የትግራይ ልዩ ኃይል ገለልተኛ አካል ቢሆንም በCOHA ውስጥ የተመለከተውን የማፍረስ ሂደት የመቆጣጠር ሃላፊነት ያለበት TIA ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ጌታቸው በደብረፂዮን ስር የሚገኘውን የህወሀት ቡድን ክልሉን በማተራመስ እና “መፈንቅለ መንግስት” ለማድረግ ሞክሯል ሲሉ ከሰዋል።

አሁን ያለው ቀውስ ካለፈው አመት ጀምሮ በህወሓት ውስጥ በተፈጠሩ የሰልጣን ፉክክሮች የተነሳ ጫና ነው።

እኤአ ማርች 11 እና 12 አንዳንድ የትግራይ ልዩ ኃይል አካላት ከደብረጽዮን ጋር በመሰለፍ በመቀሌ የሚገኘውን የክልሉን ራዲዮ ጣቢያ እና ከንቲባ ጽ/ቤትን እንዲሁም በኤርትራ ድንበር ላይ የሚገኙ በርካታ ከተሞችን፣ የሰሃርቲ ወረዳን እና የትግራይ ሁለተኛ ትልቅ የህዝብ ማእከል የሆነውን አዲግራትን ተቆጣጥርዋል። አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግስት ድጋፍ እንዲደረግላቸው በጠየቁበት ወቅት ማርች 10 ላይ ሦስት የትግራይ ልዩ ኃይል አዛዦችን ከሥራ አግደዋል። በተጨማሪም ኤርትራ የትግራይን የፖለቲካ ቀውስ እንዳትጠቀም አስጠንቅቀዋል።

ማሳሰቢያ፦ የቁጥጥር ቦታዎች ስያሜዎች ገላጭ ናቸው እና እንደ ጂኦግራፊያዊ ትክክለኛ ቦታዎች ተደርገው መተርጎም የለባቸውም።

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ (ከሁለቱ የTIA ምክትል ፕሬዚዳንቶች አንዱ እንዲሁም የሰላም እና ደህንነት የካቢኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ) እና ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (ሌላኛው ምክትል ፕሬዝዳንት እና የትግራይ ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥ) የ ትግራይ መከላከያ ሃየልን (TDF) ገለልተኝነት ደጋግመው ገለዋል። ጄኔራል ጻድቃን ትግራይ ሌላ ጦርነትን ማስተናገድ ፈጽሞ እንደማትችል እና ከግጭት የሚከላከሉ መንገዶችን ሁሉ በአስቸኳይ ሊከተሉ ይገባል ሲሉ አስጠንቅቋል። ይህ ደግሞ ክልሉ ተመልሶ ወደ ግጭት ሊገባ ይችላል ብለው በመፍራት እህል ማከማቸት እና ከባንክ ገንዘብ ማውጣት የጀመሩትን የብዙ የትግራይ ተወላጆችን አስተያየት ያስተጋባል።

ትግራይ ለኤርትራ ካለው ቅርበት እና የኤርትራ ወታደሮች የCOHAን ስመመነት በመጣስ የትግራይን  አንዳንድ አካባቢዎች እንደያዙ ከተዘገበ በኋላ በትግራይ መሪዎች መካከል በሚካሄደው የቡድን ጦርነት ውስጥ ኤርትራ ጣልቃ ልትገባ ትችላለች የሚል ስጋት አለ። እንዲሁም በድንገት ወደ ትግራይ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥር እንደ ቅስቀሳ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፤ ይህም ወደ የተሳሳተ ስሌት እና ክልላዊ ግጭት ሊዳርግ ይችላሌ ። ኤርትራ በበኩሏ ዜጎቿ ሊፈጠር ለሚችል ቅስቀሳ እንዲዘጋጁ ምልክት ሰጥታለች።

እየተፋፋመ የቆየው ውጥረት

የ ትግራየን ከልል ኣስተዳደር ዉስጥ የተፈጠረው ውጥረት ከጀመራ ኣንደ ኣመት ሞልቶታል

እኤአ ኦገስት 2024 ላይ በተካሄደው የህወሓት ኮንግረስ ደብረፂዮን የህወሓት መሪ ሆኖ ተመርጦ ጌታቸውን ጨምሮ በርካታ አመራር አባላት ታግደው በመጨረሻም ተባረው ነበር። አቶ ጌታቸው TIA ከፓርቲ ወገንተኝነት ውጪ ለማስተዳደር የሚያደርገውን ጥረት አንዳንዶች በፓርቲው ውስጥ የፀረ-ህወሓት አቋም ብለው በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል ብለዋል።

በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በየአካባቢው ትይዩ አስተዳዳሪዎችን እየሾመ ነው።

ከኦገስት ጀምሮ በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በክልሉ ዙሪያ ሌሎች የአካባቢ አስተዳዳሪዎችን በመሾም በTIA የተመረጡ አመራሮች ከስልጣን እንዲወርዱ ኣድርገዋል።

በ እኤአ ሴፕቴምበር 2024 ላይ ደብረጽዮን የትግራይ ልዩ ኃይል የሚንቀሳቀሰው በTIA አመራር ስር ነው< የሚለውን የአቶ ጌታቸውን አባባል ተቃወመው ነበር። ደብረጽዮን የመከላከያ ሰራዊቶች ትዕዛዝ ከጊዜያዊ አስተዳደር ስልጣን በላይ ነው ሲሉ ተከራክሯል። በግልጽ ባይገለጽም ይህ አቋም የትግራይ ልዩ ኃይል ሥልጣን በትክክል በህወሓት ላይ እንዳለ ይገልጻል።

እኤአ ጃንዋሪ 2025 ላይ 200 የትግራይ ልዩ ኃይል አመራሮች በደብረፂዮን ከሚመራው የህወሃት ቡድን ጋር በመጣመር TIA አንዲፈርስ አና  እንዲዋቀር ጠይቀዋ  ነበር።

የህወሓትን ቅሬታ የበለጠ ያባባሰው ደግሞ በCOHA መሰረት የድጋሚ ምዝገባው አካል ሆኖ በተመደበው የ6 ወር የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ባለማድረግ ምክንያት ፌብሩዋሪ 2025 ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለ3 ወራት ማገዱ ነው።

ለጦርነት ያለ እንቅስቃሴ?

ከ2020 እስከ 2022 ከህወሓት ጋር በተደረገው ጦርነት ላይ ኤርትራ ከፌዴራል መንግስት ሃይሎች ጋር በመሆን በመፋለም በኤርትራ ድንበር የሚገኙ የኢሮብ እና የሸራሮ ወረዳዎችን በከፊል መቆጣጠሩን ቀጥሏል። የኤርትራ ኃይሎች መገኘት ሁሉም የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ የሚያዘውን የCOHA መስፈርት መጣስ ነው። ይህ ለትግራይ ተወላጆች ብስጭት የፈጠረ ሲሆን ኤርትራ በትግራይ ዳግም ውህደት ሂደት ውስጥ አጥፊ ልትሆን ትችላለች የሚል ስጋት ፈጥሯል።

ኤርትራ በኤርትራ ድንበር የሚገኙትን የኢሮብ እና የሸራሮ ወረዳዎችን በከፊል አሁንም መቆጣጠሩን ቀጥሏል።

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ በታጠቁ ሃየሎች ግጭቶች የተወጣጠረ ቢሆንም የፌደራል መንግስት ተጨማሪ ሃይሎችን በማንቀሳቀስ ትግራይ እና ኤርትራን በሚያዋስነው አፋር ክልል ላይ ማድረጉ ተዘግቧል። ነገር ግን፣ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ  ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ኤርትራን የማጥቃት ዓላማ እንደሌላት ገልፀው ኤርትራዊያንን “ወንድማማች እና ደግ ህዝብ” ሲሉ ገልፀዋል።

እንዲሁም የክልሉን መልሶ ግንባታ በመደገፍ እና ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግርን በማረጋገጥ ላይ የፌዴራል መንግስት ቁርጠኝነትን አረጋግጠዋል። አብይ በትግራይ የሚገኝ የተለየ የፖለቲካ ቡድንን ከመደገፍ ይልቅ መንግሥት ከTIA ጋር አመራሩ ምንም ይሁን ምን እንደ አንድ አካል ሆኖ ለመሳተፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

COHA ያለበት ደረጃ

በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የCOHA ስምምነት መፈራረም ከተደረገ በኋላ የከባድ መሳሪያዎች ትጥቅ መፍታት፣ የብሔራዊ የሽግግር ፍትሃዊ ፖሊሲ መቋቋም እና ለአብዛኛው ክልል የሰብአዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን በማስፋፋት ላይ ትልቅ እድገት ታይቷል። ነገር ግን፣ የCOHA አንዳንድ ገፅታዎች አፈጻጸም መጏተቱ  በትግራይ የፖለቲካ አመራር ውስጥ እየተባባሰ የመጣውን ችግር አመላካች ነው። እነዚህም በስምምነቱ ውስጥ ካሉት 15 አንቀጾች በ4ቱ ላይ ያተኮሩ ናቸው።

አንቀፅ 5(3) – የሰብአዊ አቅርቦት፦ የተፈናቀሉ ዜጎች እና ስደተኞችን ወደ ቀያቸው መመለስ

በጦርነቱ ማጠቃለያ ላይ ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው የመጡ ወደ 2.1 ሚሊዮን የሚገመቱ ተፈናቃዮች (IDPዎች) ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከ እኤአ ጃንዋሪ 2025 ጀምሮ ወደ ትውልድ መንደሮቻቸው ተመልሰዋል ነገር ግን ኣሁንም ወደ 870,000 የሚጠጉ ተፈናቃዮችን የመመለስ አና የማዋሃደ ሂደት አልተፍጸመም። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የሚገኙት በክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ ነው። በዚህም የተበሳጩት መቀሌ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለክልል እናለፌዴራል ባለስልጣናት ተቃውሞዋቸውን ኣሰምታዋል።

አብዛኞቹ ቀሪ ተፈናቃዮች የተፈናቀሉበት የምዕራብ ትግራይ የስልጣን ወሰን ላይ የሚነሳው አከራካሪ የፖለቲካ ጥያቄ መመለሳቸውን ውስብስብ ያደርገዋል። ሁለት ኣመት በቆያው ጦርነት ወቅት የምዕራብ ትግራይ በ ኣማራ አና በ ትግራይ ታጣቂዎች መካከል በጣም አስከፊ የሆነ ጦርነት አስተናግዷል ። የአማራ ክልል ወልቃይት-ጸገዴ-ሰቲት-ሁመራ ብሎ የሚጠራውን ግዛትየሁለቱም ክልሎች ባለስልጣናት ይገባኛል ይላሉ። የአወዛጋቢው ግዛት ሁኔታ በCOHA ውስጥ አልተገለፀም፣ ነገር ግን ጠ/ሚ አብይ በህዝበ-ውሳኔ ሁኔታውን ለመወሰን ሀሳብ አቅርበዋል። የዚህ ትግበራ ችግር ያለበት ቢሆንም፣ ብዙ የቀድሞ ነዋሪዎች በመፈናቀላቸው እና ግዛቱ አሁን በታሪክ የአማራ ነው በሚሉ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በመተዳደር ላይ ናቸው።

A.Internally displaced persons (IDPs) gather under a large concrete statue of a dove as they check their names for food distribution inside a school ground used as shelter at the NSPS IDPs camp in Adwa, Tigray region.

በአድዋ፣ ትግራይ በሚገኘው እንደ ተፈናቃይ መጠለያ ባገለገለ የትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሆነው ለምግብ ማከፋፈያ ስማቸውን ሲያረጋግጡ የነበሩ የተፈናቀሉ ወገኖች በትልቅ እርግብ የኮንክሪት ሐውልት ስር ይሰባሰባሉ። (ፎቶ፦ AFP/Michele Spatari)

አንቀጽ 6 – ትጥቅ መፍታት፣ ማሰባሰብ እና መወሃድ (DDR)

ከባድ የጦር መሳሪያዎች ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በፍጥነት የተካሄደ ሲሆን ይህም የCOHA መፈረም ተከትሎ እንደተጠናቀቀ በስፋት እየተነገረ ነው።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አንድ አካል ሆኖ DDR ከየውጭ ኃይሎች እና ከትግራይ ልዩ ኃይል ውጭ የሆኑ ኃይሎች እንዲወጡ ማድረግ ነበረበት።

ወታደሮችን ማሰባሰብ እና መልሶ ማቋቋም ቀስ በቀስ እየተከሄደ በሆንም በCOHA ስምምነት መስረት የDDR ትግበራ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ልዩ ኃይሎች ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ጋር በመሆን ክትትል ሊደረግበት ይገባል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የሚደገፈው የብሄራዊ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚሽን 274,000 የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትን (ከ372,000 የቀድሞ ታጣቂዎች ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ) ለይቷል። ከእነዚህ ውስጥ 55,000 ከእንቅስቃሴ ውጪ ሆነዋል። ተጨማሪ 75,000 የህወሓት የቀድሞ ታጣቂዎች የሁለተኛው ምዕራፍ አካል መሆናቸው ታውቋል። ሂደቱ ግን በገንዘብ እጥረት እና በህወሓት ውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ሽኩቻ ምክንያት ዘግይቷል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ አንድ አካል ሆኖ DDR ከየውጭ ኃይሎች እና ከትግራይ ልዩ ኃይል ውጭ የሆኑ ኃይሎች እንዲወጡ ማድረግ ነበረበት። የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ አንዳንድ አዋሳኝ ቦታዎችን በመያዛቸው የትግራይ ተወላጆች ዋነኛ አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል። በምዕራብ ትግራይ የግዛት ክልል ውስጥ የአማራ ኃይል መቆየቱ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያለውን ቅሬታ እና ጭንቀት የበለጠ አባብሶታል።

አንቀጽ 8 – ዓለም አቀፍ ድንበሮች እና የፌዴራል ተቋማት

COHA የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልልን ጨምሮ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲያስከብር ጠይቋል። በግጭቱ ወቅት ከሚታየው ያነሰ የሚታይ ቢሆንም በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በኢሮብ፣ በጉሎማካዳ እና በሽራሮ ወረዳዎች ላይ የኤርትራ ጦር ኃይሎች መቆየታቸው ይህ ድንጋጌ እስካሁን ሙሉ በሙሉ እንዳልተሟላ ያሳያል። በእነዚህ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በኤርትራ ኃይሎች ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና ይህን የፍርሃት ድባብ እንዲቀጥል አድርጓል።

አንቀጽ 9 – በትግራይ ክልል የፌደራል ሥልጣንን ወደነበረበት መመለስ እና በፌዴራል ተቋማት ውክልና መስጠት

ያልተፈታው ጉዳይ ህወሓት ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እንዴት እንደሚዋሃድ ነው።

በCOHA ውል መሰረት ሌሎቹ ድንጋጌዎች ከተሟሉ በኋላ የፌደራል መንግስት በብሔራዊ ፌዴራላዊ ተቋማት ውስጥ የትግራይን ዳግም ውህደት እና ውክልና የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። TIA የተቋቋመው ይህ ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ ክልሉን በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድር ነው። በመጀመሪያ የ2 ዓመት የጊዜ ሰሌዳ ይኖረዋል ተብሎ የተጠበቀው የTIA ሥልጣን የCOHA ሌሎች አካላት መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ ለሦስተኛ ዓመት ተራዝሟል።

የአንቀጽ 9 ያልተፈታ ችግር ህወሓት እንዴት ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እንደሚዋሃድ ነው። እኤአ ጃንዋሪ 2021 ላይ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ህወሓት በምርጫ ቦርድ ከህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ። ግጭቱ ካበቃ በኋላ ህወሓት ከጦርነት በፊት ወደነበረበት ህጋዊ ሁኔታ እንዲመለስ ደጋግሞ ሲጠይቅ ቆይቷል። እኤአ ማርች 2024 ላይ የህወሓት በአሸባሪነት መፈረጅ የተሰረዘ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ግን በተሻሻለው የፓርቲ ምዝገባ እና የስነምግባር ማሻሻያ ረቂቅ ህግ መሰረት እንደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመዘገብ አስገድዶታል። በደብረፂዮን የሚመራው የህወሃት አመራር ግን እንደገና መመዝገብ የሚለውን ሃሳብ የፓርቲያቸውን መብት እንደጣሰ በመቁጠር ውድቅ አድርገውታል።

በክልል እና በዓለምአቀፍ ተዋናዮች የሚደረግ ሽምግልና

COHA የተፈረመው በአፍሪካ ህብረት አካላት ሥር በበይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን (ኢጋድ)፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እና በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ነው። ውጥረቶቹን ለማርገብ የአፍሪካ ህብረት ፈራሚዎችን እና አስታራቂዎችን በመጥራት እኤአ ፌብሩዋሪ 2025 ውስጥ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ውይይት አድርጓል። የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሉሴን ኦባሳንጆ የCOHA መሪ የአፍሪካ ህብረት አስታራቂ ሆነው ያልተፈቱ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል ነገር ግን የሰላሙን ሂደት ማሳነስ ወይም መቀልበስ የለባቸውም ብለወል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ቀጣይ ስብሰባ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ዋና ጸሐፊ ኢልዜ ብራንድስ ኬህሪስ የኤርትራ መከላከያ ኃይሎች በመውጣታቸው ላይ የCOHA ደንብ ቢገልጽም በትግራይ ውስጥ ቆይተዋል፣ እንዲሁም ወደፊት የሚደርሱትን ግፎች ለመከላከል እና የሰላም ሂደቱን እንዳያደናቅፍ በአፋጣኝ ለቀው እንዲወጡጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ትግራይን ጎብኝተው ልዩነቶችን በሰላማዊ ውይይት የመፍታትን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የቀጠናዊ ግጭት ስጋቶች

በ2020-2022 በትግራይ ግጭት ወቅት እንደታየው እንደገና ብጥብጥ በፍጥነት ሊባባስ እንዲሁም በትግራይ እና በሰፊው ቀንድ ላይ አስከፊ መዘዝ ያስከትላል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገሮች ከ2022 በበለጠ ያልተረጋጉ ናቸው፣ይህም የተወሳሰቡ እና ያልተጠበቁ መዘዞችን ስጋት ላይ ይጥላል። ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ከፍተኛ ግጭቶች ገጥሟቸዋል። በሱዳን ተቀናቃኝ ጄኔራሎች መካከል ያለው ጦርነት በዓለም ላይ እጅግ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል። የተለያዩ የባህረ ሰላጤው ሀገራት እና ሌሎች የውጪ ተዋናዮች የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው የሱዳንን ውዝግብ ወደ ክልላዊነት መቀየሩ የዚህን ግጭት ዋጋ እና የቆይታ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ከፍ አድርጎታል። በትግራይ ዳግም ግጭት ውስጥ ተመሳሳይ ለውጥ ቢመጣ፣ አለመረጋጋት ሊፈጠር ይችላል፣ ይህም ከ2022 ጀምሮ የተካሄደውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገትና የመልሶ ግንባታ ኢንቨስትመንቶች ይጎዳል።

በርካታ የታጠቁ ተዋናዮች በቅርበት ባሉበት፣ የፖለቲካ አጥፊዎች የተሳሳተ ስሌት እና ቅስቀሳ አደጋው ከፍተኛ ነው።

ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ ሁኔታዎችን መባባስ የሚፈልጉ አይመስሉም። ነገር ግን፣ በርካታ የታጠቁ ተዋናዮች በቅርበት ባሉበት፣ በፖለቲካ አጥፊዎች የተሳሳተ ስሌት እና ቅስቀሳ አደጋው ከፍተኛ ነው። ይህ ደግሞ እየተስፋፋ የመጣውን የንግድ ግንኙነቶቿን ለመደገፍ የበለጠ ሊገመት የሚችል የባህር ወደብ መዳረሻ በመሻት ላይ ያለችውን የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያወሳስብ ነው፣ ይህም ዓላማው ኤርትራ በቀይ ባህር የአሰብ ወደብ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ሊሆን ይችላል በማለት ታየዋለች

በህወሃት ውስጥ ያለው የእርስ በርስ ፉክክር የተፈጠሩት ውጥረቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ በመምጣት በCOHA ሸምጋዮች የሚደረግ አስቸኳይ ተሳትፎ አስፈላጊነትን ከፍ አድርጎታል። በትግራይ ተወላጆች መካከል የሚነሱ ትክክለኛ ቅሬታዎችን ለመፍታት የተደረገው ጥረት ሰፋ ባለ ሁኔታ ውስጥ በመካሄድ ላይ ሲሆን ትግራይን ወደ ኢትዮጵያ በሄራዊ ፌዴራላዊ አስተዳደር ሞዴል ውስጥ እንደገና ለማዋሃድ የሚያስችል መንገድ በመፈለግ ላይ ያለመ ነው። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በትግራይ መሪዎች መካከል ቀጣይነት ያለው ውይይት እንዲካሄድ ስለሚያስገድድ ጊዜ ይወስዳል። ይህ ሂደት እንዲቀጥል ጊዜ እና ቦታ መፍጠር ለአሸማጋዮች ትልቁ የቅርብ ጊዜ አላማ ነው።


ተጨማሪ ማጣቀሻዎች